Sunday, 14 May 2017

ጸሃይ ቆርቆሮ ማስታወቂያ







                ይህ ማስታወቂያ ሲስተዋወቅ የምርቱን ደካማ ጎን ያስተዋውቃሉ ።ይህ ደግሞ ተገቢ ኣይደለም።ይህም ማለት ሴትየዋ  ስታስተዋውቅ በጣም በመደንገጥ ድንገት አደጋ በእርሷ ላይ የደረሰባት ያክል በማስመሰል ቤትዋ በዚህ በጸሃይ ቆርቆሮ የተሰራ ቤት ሲሆን ቆርቆሮው በጣም ፎርጅድ ከመሆኑ የተነሳምለባው ቆርቆሮውን ሰብሮ በመግባት የዘረፋት በማስመሰል ታስተዋውቃለች።
              በመሆኑም እርሷ ስታስተዋውቅ ከጭሆቷም የተነሳ የሰፈር ሰዎች ሰምተው ወደ እርሷ በመሄድስለ ጭሆቷ ሲያናግሯት እሄው ሌባ ዘረፈኝ በዚሕ  ቆርቆሮ ቤቴን ባልሰራ ለዝርፊያ ኣልጋለጥም ነበርበማለት የቆርቆረውን ጥራት እያዋደቀች ትናገራለች።ነገር ግን ሴትየዋ ስታስተዋውቅ ስለቆርቆሮውብቻ ሳይሆን ስለሌባው ህገ ወጥ ስራም እግረ መንገዷን ታስተዋውቃለች።
            ስለዚህ በዚህ ማስታወቂያ ለመግለጽ የተሞከረው የሌሎችን ኣምራች ድርጅቶች ምርቶችን
ለማንቋሽሽ እና በደንበኞች ዘንድ ተቀባይነት እንዳይኖረው ለማድረግ እና ለማወዛገብ የተመሰረተማስታወቂያ ነው ቢባል ኣያጠ ራጥርም ።ምክንያቱም በሃገራችን ኣብዛኛወቹ ማስታወቂያወች ሲስተዋወቁየምርታቸውን እናየድርግታቸውን ዝና ከፍከፍ  ማድረግ እንጅ የማጣጣል እና የማንቋሸሽ ባህሪ ኣያንጸባርቁም።
                   በኣጠቃላይ በዚህ ማስታወቂያ ለመግለጽ የተሞከረው ኣንድ ማስታወቂያ ሲያስተዋውቁ ኣንድድርጅት  ያመረተውን ምርት ደካማ ጎኑን ይሁን  ጠንካራ ጎኑን እራሱ  ማስተዋወቅ ኣለበት እንጅ በሌላ ድርጅት የተመረቱ ምርቶችን ያለምንም   ፍቃድ ሲያስተዋውቁ ቢገኙ በህግ እንደሚያስቀጣ ሲያስረዳ ነው ።በመሆኑም’’የእኛ ምርት ያልሆኑ ተመሳሳይ ምርትችን የሚያመርቱ ግለሰቦችን ደርሰንባቸዋል ጉዳዩን በህግ የያዝነው ቢሆንም ብለው  ይገልጻሉ።




No comments:

Post a Comment