Tuesday, 6 June 2017
ሰላም ባስ
በሰላም ባስ ሲሄዱ አይነጠንጥም ወንበሩ ሰላም ይሰጣል መንገዱ ።ካሰቡት ቦታ ያለምንም ድካም ለመድረስ ሰላም ባስ ተመራጭ ነው ።ሰላም ባስ እውነትም ሰላም አለው ሹፌሩም አስተዋይ ነው ።በተላይም ለተማሪወች ሰኔ እና መስከረም ላይ ታላቅ ቅናሽ ያደርጋል ።ካሰቡት ቦታ ለመድረስ ከምንም በላይ ያስባል።የነገ አለኝታወች ሃገር ተረካቢወች ተማሪወች ናቸው ብሎ ያምናል። ስለዚህ ተማሪወችን በታላቅ ቅናሽ ሳይቸገሩ ካሰቡት ቦታ በሰላም ያደርሳል።ሰላም ባስ ለተማሪወች ሰላም ይሰጣል ።የትራንስፖርት ብር የሌላቸው ተማሪወችን ይተባበራል። የተማሪወችን ችግር በፍጥነት ይረዳል።ሰላም ባስ ለተማሪወች ይጨነቃል።ከፈለጉት ለማድረስ ታልቅ ቅናሽ ያደርጋል።
Sunday, 4 June 2017
ንፋስስልክ የግድግዳ ቀለም ማስታወቂያ
ይህ ማስታወቂያ በቲቪ ከሚስተዋወቁት ማስታወቂያወች አንዱ ነው።በመሆኑም ይህ ቀለም ሲስተዋወቅ
በሰወች ላይ ተጽእኖ የሚያደርስ ማስታወቂያ ነው ። ምክንያቱም በዚህ
ማስታወቂያ ላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ሴትየዋ ለመጋበዝ ተጠርታ ከሄደችበት ቤት በዚህ ቀለም የተዋበ ቤት በማየቷ የበታችነት ስሜት
እንደተሰማት ያሳያል። ስለሆነም ይች ሴት ጓደኘዋ መቼ ነው አንችስ የምትጠሪኝ ብላ ስትጠይቃት እኔ ቤቴን በንፋስ ስልክ ቀለም ካልቀባው
አልጠራሽም አለቻት።ስለዚህ ህይ ማስታወቂያ ደንበኛ ለመሳብ የቀረበ ማስታወቂያ ቢሆንም በሴትየዋ ላይ ግን ከፍተኛ የሆነ ተጽእኖ
አድርሶባታል።
በመሆኑም በሴትየዋ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ሰወችም ተጽእኖ ያደርሳል ።ነገር ግን በማሳወቂያው ለመግለጽ እንደተሞከረው በዚህ ቀለም ባይቀባ ቤት እንግዳ ማስተናገድ አይችልም ማለት አይደለም።ለምን
ይህ ይሆናል አንድ ሰው ባለው የኑሮ ደረጃ መኖር አለበት እንጅ እዴት የሌለውን ማድረግ ይችላል።አንዳንዴም ይህ ማስታወቂያ ሰው
እንደ ቤቱ እንጅ እንደ ጎረቤቱ አይኖርም በሚለው ምሳሌያዊ አነጋገርም ይተቻል።
ከዚህም ባለፈ አንድ ሰው
በራሱ መተማመን እና በራሱ እራሱን መምራት አለበት እንጅ በሰወች ጥገኛ መሆን የለበትም ። ስለዚህ በዚህ ማስታወቂያ ለመግለጽ እንደተሞከረው
ያለ ቀለም ቤት ምንም ዋጋ እንደሌለው ያስረዳል።ነገርግን በመጀመሪያቤት ሲሰራብዙ የሚያስፈልጉት ነገሮች አሉት ። በመሆኑም እነዚህ መሰረታዊ የሆኑ መስሪያወች ካልተሟሉ እና
ቤቱ ካልተሰራ ቀለም ብቻውን ለምንም አገልግሎት አይውልም። ስለዚህ ይህ ማስታወቂያ ሲስተዋወቅ እነሱ የራሳቸው ምርት እንዲሸጥላቸው እንጅ የሰወችን ስብእና ለመጠበቅ ምንም
አይነት ዘዴ አልተጠቀሙም። አንዳንዴም ምንም አይነት ገቢ ሳይኖረን በስሜት ያለንን ሃብት ለቀለም ብቻ የምንጠቀመው ከሆነም ይህ
ተገቢ አይደለም ።
በአጠቃላይ በዚህ ማስታወቂያ
የቀረበው አገላለጽ በሰወች ላይ ተጽእኖ እንደሚያደስ እና በተለይም ከስነምግባር አንጻር ሲታይ በጣም
የወረደ እና በሰወች ላይም የሞራል ጉዳት የሚያደርስ መሆኑ አያጠራጥርም።
ምክንያቱም ይህ ማስታወቂያ የአንድን ሰው ሃብት ከሌላ ሰው ጋር የሚይወዳድር እንጅ ሰወች በራሳቸው አቅም እንዲገዙ እና እንዲጠቀሙ
የሚያስተናግድ እንኳ አይመስልም።
Subscribe to:
Posts (Atom)