Tuesday, 6 June 2017

ሰላም ባስ


በሰላም ባስ  ሲሄዱ አይነጠንጥም ወንበሩ ሰላም ይሰጣል መንገዱ ።ካሰቡት ቦታ ያለምንም ድካም ለመድረስ ሰላም ባስ  ተመራጭ ነው ።ሰላም ባስ እውነትም ሰላም አለው ሹፌሩም አስተዋይ ነው ።በተላይም ለተማሪወች ሰኔ እና መስከረም ላይ ታላቅ ቅናሽ ያደርጋል ።ካሰቡት ቦታ ለመድረስ ከምንም በላይ ያስባል።የነገ አለኝታወች ሃገር ተረካቢወች ተማሪወች ናቸው ብሎ ያምናል። ስለዚህ ተማሪወችን በታላቅ ቅናሽ ሳይቸገሩ ካሰቡት ቦታ በሰላም ያደርሳል።ሰላም ባስ ለተማሪወች ሰላም ይሰጣል ።የትራንስፖርት  ብር የሌላቸው ተማሪወችን ይተባበራል። የተማሪወችን ችግር በፍጥነት ይረዳል።ሰላም ባስ ለተማሪወች ይጨነቃል።ከፈለጉት ለማድረስ ታልቅ ቅናሽ ያደርጋል።

Sunday, 4 June 2017

ንፋስስልክ የግድግዳ ቀለም ማስታወቂያ









ይህ ማስታወቂያ በቲቪ ከሚስተዋወቁት ማስታወቂያወች አንዱ ነው።በመሆኑም ይህ ቀለም ሲስተዋወቅ በሰወች  ላይ ተጽእኖ የሚያደርስ ማስታወቂያ ነው ። ምክንያቱም በዚህ ማስታወቂያ ላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ሴትየዋ ለመጋበዝ ተጠርታ ከሄደችበት ቤት በዚህ ቀለም የተዋበ ቤት በማየቷ የበታችነት ስሜት እንደተሰማት ያሳያል። ስለሆነም ይች ሴት ጓደኘዋ መቼ ነው አንችስ የምትጠሪኝ ብላ ስትጠይቃት እኔ ቤቴን በንፋስ ስልክ ቀለም ካልቀባው አልጠራሽም አለቻት።ስለዚህ ህይ ማስታወቂያ ደንበኛ ለመሳብ የቀረበ ማስታወቂያ ቢሆንም በሴትየዋ ላይ ግን ከፍተኛ የሆነ ተጽእኖ አድርሶባታል።


በመሆኑም በሴትየዋ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ሰወችም  ተጽእኖ ያደርሳል ።ነገር ግን በማሳወቂያው ለመግለጽ እንደተሞከረው  በዚህ ቀለም ባይቀባ ቤት እንግዳ ማስተናገድ አይችልም ማለት አይደለም።ለምን ይህ ይሆናል አንድ ሰው ባለው የኑሮ ደረጃ መኖር አለበት እንጅ እዴት የሌለውን ማድረግ ይችላል።አንዳንዴም ይህ ማስታወቂያ ሰው እንደ ቤቱ እንጅ እንደ ጎረቤቱ አይኖርም በሚለው ምሳሌያዊ አነጋገርም ይተቻል።


 ከዚህም ባለፈ አንድ ሰው በራሱ መተማመን እና በራሱ እራሱን መምራት አለበት እንጅ በሰወች ጥገኛ መሆን የለበትም ። ስለዚህ በዚህ ማስታወቂያ ለመግለጽ እንደተሞከረው ያለ ቀለም ቤት ምንም ዋጋ እንደሌለው ያስረዳል።ነገርግን በመጀመሪያቤት ሲሰራብዙ የሚያስፈልጉት  ነገሮች አሉት ። በመሆኑም እነዚህ መሰረታዊ የሆኑ መስሪያወች ካልተሟሉ እና ቤቱ ካልተሰራ ቀለም ብቻውን ለምንም አገልግሎት አይውልም። ስለዚህ ይህ ማስታወቂያ ሲስተዋወቅ  እነሱ የራሳቸው ምርት እንዲሸጥላቸው እንጅ የሰወችን ስብእና ለመጠበቅ ምንም አይነት ዘዴ አልተጠቀሙም። አንዳንዴም ምንም አይነት ገቢ ሳይኖረን በስሜት ያለንን ሃብት ለቀለም ብቻ የምንጠቀመው ከሆነም ይህ ተገቢ አይደለም ።


 በአጠቃላይ በዚህ ማስታወቂያ የቀረበው አገላለጽ በሰወች ላይ ተጽእኖ እንደሚያደስ እና በተለይም ከስነምግባር አንጻር  ሲታይ  በጣም የወረደ እና  በሰወች ላይም የሞራል ጉዳት የሚያደርስ መሆኑ አያጠራጥርም። ምክንያቱም ይህ ማስታወቂያ የአንድን ሰው ሃብት ከሌላ ሰው ጋር የሚይወዳድር እንጅ ሰወች በራሳቸው አቅም እንዲገዙ እና እንዲጠቀሙ የሚያስተናግድ እንኳ አይመስልም።

Tuesday, 23 May 2017

አክስ ዶድራንት ማስታወቂያ




ይህ ማስታወቂያ እንደምናየው የሚያመለክተው ወንዱ ሰውየ ዶድራንቱን ተቀብቶ ሴቶቹን በዶድራንቱ ሽታ ሲስባቸው እና ወደ እርሱ  ሲስባቸው እና ወደእርሱ ቀርበው ከእርሱ ጋር ሆነውው እናያቸዋለን።በመሆኑም በዚህ ማስታወቂያ ለመግለጽ እንደተሞከረው የኦድራንቱን ጥራት ለመግለጽ ሲሉ በዚህ ስእል መስለው አቅርበውታል። ይህም ለሚገልጸው ሰውየው ዶድራንቱን አንደተቀባ ሁለት እና ከዚያም በላይ የሆኑ ሴቶች በአንድ ጊዜ ወደ እርሱ እንደሚሄዱ ያመለክታል።ይህም ሲባል የዶድራንቱ ሽታየሚያምር እና የሚስብ መሆኑን ይገልጻል።
ነገር ግን በዚህ ማስታወቂያ ለመግለጽ እንደተሞከረው አንድ ወንድ ከሴቶች ጋር ለመኖር እና ሴቶች ለእርሱ ጥሩ አመለካከት  ወይም ጥሩ እይታ እንዲኖራቸው የግድ አክስ ዶድራንትን መጠቀም አለበት ቢባል ወደኋላ የሚያስብል አይደለም ።በመሆኑም ይህ ማስታወቂያ የዶድራንቱን ጥራት ለመግለጽ የተሰራ ቢሆንም በተዘዋዋሪ ግን በወንዶች እና በሴቶች ላይ ተጽእኖ አሳድሯል ቢባል አያሳፍርም። ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ እንደሚያሳየው አንድ ወንድ ሴቶችን ለመሳብ የግድ ዶድራንት መቀባት አለበት እንጅ ያለ ዶድራንት አንድም ሴት እንደማይቀርበው ያንጸባርቃል።
 ይሁን እንጅ አንድ ሰው ወንም አንድ ወንድም ከሴቶች ጋር ለመኖር ወንም ሴቶችን ለመቅረብ ቢፈልግ እንኳን በጥሩ ስነምግባር እና ስብእና መቅረብ አለበት እንጅ ዶድራንትን የእርሱ መገለጫ ማድረጉ እርሱነቱን ሊገልጽለት አይችልም።ይህም ሲባል አንድ ሰው የራሱ የሆነ ስነምግባር አለው በመሆኑም ይህ ሰው አክስ ዶድራንት ምርጫው ከሆነ ለእራሱ መጠቀም አለበት እንጅ እርሱ የተጠቀመው ለሌሎች እርካታ ሊሆን አይችልም።እንዲሁም በሌላ መልኩ ደግሞ ይህ ማስታወቂያ በሴቶች ላይ ተፅዕኖ ሲያሳድርባቸው ይታያል። ስለሆነም በማስታወቂያው ለመግለጽ እንደተሞከረው ሴቶች ዶድራንት የተቀባ ወንድ በአጣገባቸው ቢሄድ እንደማያሳልፉት ያመለክታል። ነገርግን ይህ ማስታወቂያ እንደሚገልጸው የሴቶችን ስብእና የሚጋፋ ነው ቢባል የሚገርም አይደለም።
 በአጠቃላይ በዚህ ማስታወቂያ ለመግለጽ እንደተሞከረው ወንዶች ያለ ዶድራንት የሚቀርባቸው ሴት እንደሌለ እና ሴቶች ደግሞ ዶድራንት ያልተቀባ ወንድ እንደማይቀርቡ ያመለክተናል።ያም ይሁን ይህ የሚገርመው ይህ ዶድራንት ይሁሉ ምርጫ መሆኑን እንዴት በአራት ነጥብ መደምደም ይቻላል ይህ አጠያያቂ ነው ቢባል የሚገርም አይደለም። እንዲሁም ወንዶች ሴቶችን በቀላሉ ለማግኘት እና ለመሳብ ቢፈልጉ አክስ ዶድራንትን እንደ ማባበያ መጠቀማቸው እና ሴቶች ደግሞ እንዲህ ተራ በሚባል ነገር እንደሚታለሉ የመሳሰሉትን ነገሮች በዚህ ማስታወቂያ ተንጸባርቀዋል።

Wednesday, 17 May 2017

ሚራክልየጸጉርቅባትማስታወቂያ



ሚራክልየጸጉርቅባትማስታወቂያ 
ይህ ማስታወቂያ በሬዲዮ ከሚስተዋወቁት ማስታወቂያወች አንዱ ነው።ማስታወቂያውደንበኞችን ከማሳመን አንጻር እና የነሱ ደንበኞች እነማን ናቸው ብለን ስንመለከት  በዚህ ማስታወቂያ ለመግልጽ እንደተሞከረው ሚራክል የጸጉር ቅባት ጸጉርን የሚያለሰልስ ስሮችን የሚያዳብር የሚያጠነክር እየተባለ ይስተዋወቃል።ነገር ግን አንድ ማስታወቂያ ማስታወቂያ ሊያሰኘው ይሚችለውስለምርቱ እውቅና እንዲኖረው እና የምርቱን አገልግሎት መግለጽ ብቻ አይደለም።
ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ ሲስተዋወቅ ስለ ምርቱ ጥቅም እና አገልግሎት ብቻ ሳይሆን የእኛ ምርት ተጠቃሚወች እነማን ናቸው ለማን ብናስተዋውቅ ተቀባይነት ይኖረናል ብለው ግምት ውስጥማስገባት አለባቸው ።በመሆኑም ይህ ማስታወቂያ ሲስተዋወቅ ሚራክል የጸጉር ቅባት ተብሎ መሰየሙ እንጅ ይህ የጸጉር ቅባት ለሴቶች ለወንዶች ተብሎ ግልጽ የሆነ ማብራሪያ አልተሰትጠም።
ማስታወቂያው ደንበኞችን ከማሳመን አንጻርም ስንመለከት ይህ ማስታወቂያ ሲስተዋወቅ ምንም አይነት የሚስብ እና የማሳመን ዘዴወችን አልተጠቀሙም ።ስለ ማስታወቂያው እንዲህ ብለን ካየን እስኪ ስለምርቱ እንመልከት።እንግዲህ ሚራክል የጸጉር ቅባት ከማስታወቂያው እንደሰማነው ጸጉርን የሚያሳምር የሚያለሰልስ ስሮችን የሚያጠነክር የሚያዳብር እየተባለ ይስተዋወቃል። ነገር ግን ይህ የጸጉር ቅባት ጸጉርን ከማለስለሱ እና ከማዳበሩ ይልቅ የመነቃቀል እና የመበጣጠስ ባህሪ ይታይበታል።
ስለሆነም ይህ የሚያስተዋውቁት ምርት እነርሱ የገለጹት እና ደንበኞች ተጠቅመው የሚያገኙት ጥቅም የተለያየ ነው ።በመሆኑም ይዚህ ምርት ማስታወቂያ በቀላሉ ለትችት መጋለጹ የማይቀር ነው። በአጠቃላይ አንድ ድርጅት ወይም ግለሰብ ስለአመረተው ምርት ማሰተዋወቅ ሲፈልግ የደንበኞችን ፍላጎት ምን ይመስላል የሚለውን አስቀድሞ ግምት ውስጥ ማስገባት ተገቢ  ነው።